+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር #በሳይንስ_ሙዚዬም ተጀምሯል

5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር #በሳይንስ_ሙዚዬም ተጀምሯል

የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት በሚል መሪ ቃል በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA የተዘጋጀው 5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ተወካዮች /ቤት እና የፌዴሬሽን /ቤት አባላት፣ የግል ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት #በሳይንስ_ሙዚዬ ተጀምሯል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት / ትዕግስት ሃሚድ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የሳይበር ደህንነት ወር በአለም አቀፍ ደረጃ 21 ጊዜ በሀገራችን ደግሞ 5 ጊዜ በመከበር ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የሳይበር ወር መከበር ዋና አላማ ሀገራት ለዜጎቻቸው እንዲሁም ለተቋማቶቻቸው የሳይበር ደህንነት ግንዛቤን ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መርሃ ግብሮችን ለማከናወን እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

የእለቱ የክብር እንግዳ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ክቡር አቶ ማሞ ምሕረቱ 5ተኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በይፋ አስጀምረዋል፡፡ በመክፈቻ ንግግራቸውም አለም ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በገባችበት በዚህ ጊዜ ከሳይበር ደህንነት ርእሰ ጉዳይ ውጪ ወቅታዊ እና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ሌላ አብይ ጉዳይ ሊኖር አይችልም ብለዋል። "የቁልፍ የመሠረተ ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ቃል በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተዘጋጀውን 5ኛውን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን ስናከብር ቁልፍ መሠረተ ልማት የማንኛውም ዘመናዊ ማህበረሰብ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል ቀዳሚ እንደመሆኑ መጠን የእነዚህን መሰረተ ልማቶች ደህንነታቸዉን ማረጋገጥ ባለንበት የዲጂታል ዘመን ሀገራዊ ሉዓላዊነታችንን ለመጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ ነው ሲሉ ክቡር አቶ ማሞ ምሕረቱ ገልጸዋል።

የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት

#5ተኛው_ሀገር_አቀፍ_የሳይበር_ደህንነት_ወር

ከጥቅምት 1 እስከ 30/2017 /

#የኢንፎርሜሽን_መረብ_ደህንነት_አስተዳደር

#INSA

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ