+251118132191
contact@mint.gov.et
GDOP የተሰኘ ከወረቀት ነጻ የመንግስት ዲጂታል ኦፊስ ፕላትፎርም በዛሬው እለት ተመረቀ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዲስ ያለማውን ከወረቀት ንክኪ ነጻ GDOP የተሰኘውን (Government Digital Office Platform) የመንግስት ዲጂታል ኦፊስ ፕላትፎርም የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት እስመርቋል፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ ሀገራችን ብዙ መፍትሔዎችን የሚፈልጉ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በመስራት የህዝብ ፍላጎትን ለማሟላት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እጅግ ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ እንቁ ልጆቿን እያስተማረች ነው ያሉት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሁሉንም ተቋማት ስራዎች ስለሚመለከተው ሀገራዊ መፍትሔዎችን ለማምጣትና የምንፈልገውን እድገት ለማስመዝገብ ያለንን ብቁ የሰው ሀይልን በመጠቀም በትብብር መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የሀገራዊ ተልኮቻችንን ለማሳካት ከመንግስት ተቋማት፣ ከአጋር ድርጅቶችና ከግሉ ዘርፍ ጋራ በመተባበርና በመናበብ የመንግስት ስራዎችን ማቀላጠፍና ማፋጠን የሚያስችሉ ሲስተሞችን ማልማት ላይ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡
ለሀገራችን እድገት መሰረቱ ቴክኖሎጂ በመሆኑ ያለማናቸውን ሲስተሞች እንደሀገር ሁሉም ሊጠቀምባቸው ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ ከተቋማችን ባሻገር ለሌሎች ሞዴል የሚሆኑ ቴክኖሎጂን ማሸጋገር የሚያስችሉና የኢኮኖሚ ግንባታውና የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን መሰራታቸውንም አስገንዝበዋል፡፡
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ በዝግጅቱ ላይ እንዳሉት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመንግስት አገልግሎቶችን ከማልማት አንጻር በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸው በዛሬው እለት የተመረቀው Government Digital Office Platform የተቋሙን የውስጥ አሰራር ከማዘመን ባሻገር ለሌሎች ተቋማት በአጭር ጊዜ እንዲተላለፍ መሰራት እንዳለበት ጠቅሰዋል።
ወደ መሬት የወረደ ስራ በማየቴ ደስተኛ ነኝ ያሉት ኮሚሽነሩ የለሙ ሲስተሞችን በመውሰድ ለተግባራዊነታቸው በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
በመንግስት ዲጂታል ኦፊስ ፕላትፎርም(Government Digital Office Platform)/GDOP/ምርቃት ላይ የተገኙት ከተለያዩ ተቋማት የተጋበዙ ሚኒስትሮችና የስራ ሀላፊዎች በተቋሙ የተሰሩትን የመንግስት ዲጂታል ኦፊስ ፕላትፎርም አተገባበር ፣ የዲጂታል አገልግሎቶች ስልጠና ማዕከል፣የዘመናዊ አሳ እርባታ ማሳያን፣ የህጻናት ማቆያ ማዕከልን እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።
የመንግስት አገልግሎቶችን ከማልማት አንጻር ከዚህ ቀደም በኢሰርቪስ ፖርታል ከ900 በላይ የመንግስት አገልግሎቶች የለሙ ሲሆን በዛሬው እለት የተመረቀው (Government Digital Office Platform)/GDOP/ ፕላትፎርም ማንኛውም የስራ ሃላፊ GDOPን በመጠቀም ባለበት ሆኖ ስራዎችን መስራት ፣መከታተልና መምራት የሚያስችለው ነው።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች