+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) አባል ሀገራቱን ተጠቃሚ የሚያደርግ የአፍሪካ የክላውድ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ፕሮጀክት ሊጀምር ነው።

ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ፕሮጀክት ትግበራ የገበያ ትንተና ጥናት ለማድረግ የሚያስችለውን ገንዝብ ከአፍሪካ ልማት ባንክ አግኝቷል።

የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች በኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ጋር እየተወያዩ ሲሆን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች ጋርም ተወያይተዋል።

የአፍሪካ ክላውድ አገልግሎት ስነ-ምህዳር ፕሮጀክት እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ ኢኮኖሚ፣ ግብርና፣ የመንግስት አገልግሎት የመሳሰሉ ወሳኝ ዘርፎችን ዲጂታል ለማድረግ እና በአህጉሪቱ ውስጥ አስተማማኝ የክላውድ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ይሽሩን አለማየሁ ( ኤች ) የአፍሪካ ክላውድ አገልግሎት ፕሮጀክት ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚደግፍ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

አፍሪካውያን በዲጂታል አሰራር ላይ በትብብር መስራታቸው የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ምህዳር ለማዘመን እንደሚያስችል የተናገሩት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በሁሉም ዘርፍ የሚደረግ ትብብር ወሳኝ ስለመሆኑ አብረርተዋል። ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ሀገራት ለሚገጥማቸው የአይ መሰረተ ልማት፣ ለክላውድ አገልግሎት የሚከፈል ከፍተኛ ወጪ እና በኃይል መቆራረጥ ምክንያት የመረጃ ማዕከላትን ያለማስተናገድ ችግሮች በመቅረፍ ለአባል ሀገራቱ አስተማማኝ የክላውድ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው።

ክቡር ዶ/ር  የሹሩን ዓለማየሁ

የአይሲቲና ዲጂታል ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዴኤታ

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ