+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በሀገራችን በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ዘርፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሙያ ማህበራት መፈጠር እንዳለባቸው ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ገለፁ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተለያዩ የሙያ ማህበራት ጋር በምርምርና ልማት እና የሙያ ማህበራት ጥምረት አስፈላጊነት ላይ በአካልና በበይነ-መረብ ኮንፈረንስ አካሂደዋል፡፡

ኮንፈረንሱ የሀገሪቱን ልዩ ልዩ የሙያ ማኅበራት አንድ የሚያደርግ በኢትዮጵያ ፕሮፌሽናልና ስትራቴጂካዊ የሆነ የለውጥ ራዕይ ያለው ድርጅት ለመመስረት ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ በሳይንስ፣ በምርምር፣ በፈጠራ እና በቴክኖሎጂ (STI) ዘርፍ አቅም ያለው የሙያ ማህበራት በሀገራችን መፈጠር እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በዘርፉ ላይ በጥምረት ለሚሰሩ የሙያ ማህበራት መንግስት ድጋፍ ያደርጋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የኢኖቬሽን ዘርፍ ስኬት ለማረጋገጥ ምቹ ስነ-ምህዳር ግባታ ላይ መንግስት ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

መንግስትና የግሉ ዘርፍ በተሰጦ ላይ በትብብር ሲሰሩ የሙያ ማህበራት ሚና የላቀ መሆን አለበት ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በሳይንስ፣ በጤና፣ በኢንጂነሪንግ፣ በሂሳብ፣ በግብርና፣ በትምህርት፣ በአይሲቲ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን በትብብር አቅም ፈጥረን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሀገራዊ ምርምር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሀብታሙ አበራ በሀገራዊ ምርምር ልማት የተገኙ ውጤቶችን በማጎልበት ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ልንጠቀምባቸው ይገባል ብለዋል፡፡

አክለውም የተበታተኑ የሙያ ማህበራት ወደ አንድ ጥምረት በማምጣት በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ዘርፍ ላይ ሀገራዊ ለውጥ ማምጣት እንዲችሉ ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ እውቀት አቅም ሊፈጠርላቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በኮንፍረንሱ የቀረቡትን ሀሳቦች በማጠናከር ሁሉም በየዘርፉ ወደ አንድ ጥምረት በመምጣት ችግር ፈቺ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ