+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያለን አቅም በማሳደግ ቀጣይነት ያለው ልማትና ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ መስራት ይኖርብናል፡፡ዶ/ር ባይሳ በዳዳ

የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ፣ ከአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር Ai አፕሊኬሽኖችን መጠቀም ( AI for resilient food systems) በሚል ርእስ ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡት ሀላፊዎች እና ተመራማሪዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው ማስጀመር ፕሮግራም ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያለን አቅም በማሳደግ ቀጣይነት ያለው ልማትና ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ መስራት ይኖርብናል፡ ብለዋል።

Ai የሰብል ምርትን ማሳደግ፣ የአፈር ጤና አጠባበቅ፣ ተባዮችን እና በሽታን የመቆጣጠር እና የግብርና ምርቶችን የማሳደግ አቅም ከፍ ያደርጋል ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መንግስት የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ እና ዘላቂ እና በግብርና የለማ አከባቢን ለመፍጠር እየሰራቸው ያሉ ስራዎች በቴክኖሎጂ በመደገፍ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ስልጠናው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የሳይንስ መሪዎች፣ ተመራማሪዎች እና የግብርና ባለሙያዎች አርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ ለግብርና ምርምር ማመልከቻዎች፣ ለዕፅዋት ጥበቃ፣ ለዕፅዋት ማራባት፣ ለአፈር ጤና እና ውሃ አስተዳደር፣ ለእንስሳት እርባታ ፣ ለባዮቴክኖሎጂ እና የምግብ ሳይንስ ላይ እንዴት እንደሚተገበር እና ይሀንን በመጠቀም በግብርና ምርምር እና የምግብ ምርታማነትን ለማጎልበት የሚያስችል ክህሎትን ማሳደግ ላይ ያለመ ነው።

ስልጠናው ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት እና ከ23 የምርምር ማዕከላት፣ ከኦሮሚያ ፣ ከአማራ፣ ከትግራይ ፣ ከአፋር፣ ከሶማሌ፣ ከጋምቤላ፣ ከኢትዮጵያ ማእከላዊ ክልሎች፣ ከደቡብ እና ከደቡብ ምዕራብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት እና ከግብርና ሚኒስቴር የተውጣጡ ተመራማሪዎች እና ከፍተኛ ሀላፊዎች ተሳትፈውበታል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ