+251118132191
contact@mint.gov.et
ቴክኖሎጅን መጠቀም የህልውና ጉዳይ ከመሆኑም በላይ ከ4.0 ቴክኖሎጂ ባሻገር በተወዳዳሪነት ለመዝለቅ 5.0 ቴክኖሎጅዎችን ለመከተል አልመን መስራት አለብን።(ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ)
በ3ኛው ዙር ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አምስተኛ ቀን የፓናል ውሎ ቴክኖሎጅን ከምርት ጋር በማዋሀድ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማዘመን በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተካሄዷል፡፡
በውይይት መርሀ ግብሩ በፓናሊስትነት የተሳተፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ይሹሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) ለአምራች ኢንዱስትሪዎች በዚህ ዘመን ቴክኖሎጂን መጠቀም የህልውና ጉዳይ ከመሆኑም ባሻገር አለም ወደ ኢንዱስትሪ 5.0 እየተንደረደረ ባለበት በዚህ ወቅት እኛም የኢንዱስትሪ 5.0 (አምስተኛውን የኢንዱስትሪ አብዮት) አልመን ተግተን መስራት እና በ”መፍጠንና መፍጠር” እሳቤ መንቀሳቀስ አለብን ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ዶ/ር ይሹሩን አክለውም ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም ያልቻሉ ሀገሮችም ሆነ አምራች ኩባንያዎች ከውድድር ውጭ መሆናቸውን በመጥቀስ የአምራች ኢንዱስትሪውን አሰራር ዲጂታል ማድረግና አሰራርን ማዘመን የግድ ነው ብለዋል።
ያለንበት የውድድር ዓለም ቆሞ ስለማይጠብቅ እንደ አገር አስቻይ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ መንግስት እየሰራ ሲሆን ተቋማት ተደራጅተው ወደ ስራም ገብተዋል ብለዋል።
መንግስት ፖሊሲ በመቅረጽ ስትራቴጂ በማስቀመጥ አልሞ እየሰራ መሆኑን አስታውሰው የግሉ ሴክተር የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ሲሉ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎችን አሰራር በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን ከቴክኖሎጅ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ጀምሮ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ለባለሙያዎችና ለዘርፉ አብቂዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናና ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች