+251118132191
contact@mint.gov.et
ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገራቸው በማምጣት ሊያግዙ እንደሚገባ ዶ/ር በለጠ ሞላ ገለፁ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከዮሚማ ቴክኖሎጂ ሶልሽንስ (Yomima Technology Solutions) ድርጅት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂን በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ ላይ ለመጠቀምና ተማሪወችን ከታች ጀምሮ የቴክኖሎጂው ልምምድ ኖሯቸው ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት በማሰብ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ለሀገራቸው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማበርከት ኢኮኖሚውን እንዲደግፉ ያለመ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራዎች በሚኖሩበት ሀገር ያሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገራቸው በማምጣት ቴክኖሎጂ እንዲላመድና ለሀገራዊ የእድገት አካል ሆኖ እንዲጠቀሙበት የማስቻል ሀገራዊ አደራ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ሀገርን በቴክኖሎጂ ማገዝ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ያሉት ሚኒስትሩ እንደ ዮሚማ ቴክኖሎጂ ሶልሽን (Yomima Technology Solutions) ድርጅት ባለቤት ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለሀገራቸው የሚያበረክቱትን አስተዋፆ ለማገዝና ለመተባበር ሁሌም ዝግጁ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
በአለም ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ያለውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂን ወደ ሀገር በማምጣት ተማሪወች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መሰረት እንዲይዙበት ታስቦ እየተሰራ ያለውን ፕሮጀክት ለማሳካት በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡
የዮሚማ ቴክኖሎጂ ሶልሽን ድርጅት ባለቤት ወ/ሪት ሌንሳ በፍቃዱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂን በትምህርቱ ዘርፍ ላይ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ለማሳካት ቴክኖሎጂ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡
አክለውም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ለመምህራንና ለተማሪዎች እና በሌሎችም ዘርፎች ላይ የመማር ማስተማሩን ስርዓት ለማሳለጥ የሚያስችል አፕሊኬሽን ለማበርከት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
የተካሄደው ስምምነት ወደ መሬት ለማውረድና እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አገልግሎት ላይ እንዲውሉ የትብብር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ሌሎች ዲያስፖራዎች እንዲህ ያሉ ስራዎችን ወደ ሀገራቸው እንዲያመጡና እንዲያግዙ ጥሪ ተላልፏል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች