+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት ለመገንባት ከአጋር ሀገራት ጋር በትብብር እየሰራች መሆኑን ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ ገለፁ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፈረንሳይና ከሱዳን ሪፑብሊክ ምሁራን ጋር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ስርዓትን ለማጎልበት የሚያስችል አውደ ጥናት እያካሄዱ ነው፡፡

አውደ ጥናቱ በኢትዮጵያ፣ በፈረንሳይ እና በሱዳን ሙህራኖች መካከል በትምህርት መስክ ቀጣይነት ያለው የኢኖቬሽን፣ የቴክኖሎጂና የዲጂታል የእውቀት መጋራትና የልምድ ልውውጥን በማሳለጥ የዲጂታል ኢኮኖሚውን በጋራ ለመገንባትና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለመገንባት በሚያስችሉ የትምህርት አካዳሚክ ዘርፍ ላይ ከአፍሪካና ከሌሎች አጋር አለም ሀገራት ጋር በቅንጅትና በትብብር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራች ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየሰራች ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ከፈረንሳይ የትምህርት ተቋማት በተውጣጡ ምሁራንና እና ከሱዳን ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር ዘርፉን ለማሳደግ የሚሰሩ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማጎልበት የሚካሄደው አውደ ጥናት ለሀገራቱ የላቀ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።

በሱዳን የፈረንሳይ አምሳደርና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሚስተር በርትካንድ ኮቸሪ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን ሪፓብሊክ ሀገር ዘመኑ የሚሻውን ቴክኖሎጂን ለማስታጠቅ ወጣቶችን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በማስተማር የዕውቀትና የክህሎትን መሠረት ለመጣል አዳዲስ ፕሮጀክቶችን መቅረፅና ወደ ተግባር መግባት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የሱዳን ሪፑብሊክ የኢትዮጵያ አምሳደር እየተካሄደ ያለው ወርክሾፕ በሀገራቱ መካከል ያለውን የትብብር ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያለውን ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

አውደ ጥናቱ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከፈረንሳይ ዩኒቨርሲቲዎች የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተልዕኮ ምሁራን እና ከሱዳን ሪፑብሊክ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ ምሁራን፣ ፕሮፌሰሮች፣ ከፍተኛ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በአውደ ጥናቱ በሀገራቱ መካከል የዲጂታል ቴክኖሎጂና አጠቃቀም እውቀትን ለማጎልበት የጋራ ግንዛቤ፣ የልምድ ልውውጥ፣ የምርምር፣ ፈጠራ፣ ዲጂታላይዜሽን እና የኢኮኖሚያዊ እድገትን ያበለፅጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ