+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከህንድ ኮግኒቬራ (KogniVera) የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መከሩ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከህንድ ኮግኒቬራ (KogniVera) የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማሳለጥና ፈጠራን ለማጎልበት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሹሩን አለማየሁ (ፒ ኤች ዲ) ሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በመስራት ሂደት ውስጥ የትብብር ስራዎችን ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደምትገኝ ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም ያላት ሀገር ናት ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራችን በቴክኖሎጂና በዲጂታል ዘርፉ ላይ ያላትን መሰረተ ልማት ለማጎልበትና ኢኮኖሚያችንን ለማሳደግ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር መስራቱ ወሳኝ ሚና አስገንዝበዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ እርብርብ እያደረገች ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ከስኬት ማማ ላይ ለማድረስ የሚገኙ እድሎች ሁሉ በመጠቀም በትብብርና በቅንጅት መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
የህንድ ኮግኒቬራ (KogniVera) የቴክኖሎጂ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ካምሌሽ ኩመር ከኢትዮጵያ ጋር በቴክኖሎጂና በዲጂታል ዘርፍ ላይ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በቴክኖሎጂና በዲጂታል ዘርፍ ላይ ረጅም ልምድ እንዳላቸው እና በተለያዩ ሀገራት ውጤታማ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኙ የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈፃሚው ዜጎች በዌብ ቴክኖሎጂ፣ በአፕ ልማት፣ በCloud ቴክኖሎጂ፣ AI እና ML፣ በዳታ እና በሳይበር ደህንነት እና በሌሎችም መሰረታዊ እና የላቀ እውቀት እንዲኖራቸው እንደሚሰሩ አንስተዋል፡፡
በምክክሩ ላይ ኢትዮጵያን እና ህንድ የረጅም ጊዜ ግንኙነት የነበራቸው ሀገሮች እንደመሆናቸው መጠን የሁለትዮሹን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት እንደሚሰሩም ገልፀዋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች