+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኮደርስ ስልጠና በዲጅታል ዘርፍ የኢትዮጵያን እድገት ለማሳለጥ ጉልህ ሚና አለው - አህመዲን መሃመድ (ዶ/ር)

የኮደርስ ስልጠና በዲጅታል ዘርፍ የኢትዮጵያን የምጣኔ ሃብት እድገት ለማሳለጥ ፋይዳው የላቀ መሆኑን በአማራ ክልል በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ ዶ/ር አህመዲን መሃመድ ተነናግረዋል።

በአማራ ክልል በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ የኮደርስ ስልጠና አፈጻጸም በተመለከተ በደሴ ከተማ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

አህመዲን መሃመድ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት፥ የኮደርስ ስልጠና በዲጅታል ዘርፍ የኢትዮጵያን የምጣኔ ሃብት እድገት ለማሳለጥና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ፋይዳው የላቀ ነው።

ለዚህም መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አንስተው፥ በተለይም ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና እድል ተጠቃሚ ለመሆን መትጋት አለባቸው ብለዋል።

የኮደርስ ስልጠና በእውቀት እና ክህሎት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርግ በመሆኑ አጋጣሚው እንዳያመልጥ ሁሉም ሊሰለጥን እንደሚገባ አንስተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎችና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የስልጠና ክፍል በማዘጋጀትና ግብዓት በማሟላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው በበኩላቸው፥የኮደርስ ስልጠና በቴክኖሎጂ የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

በዚህም በክልሉ ስልጠናውን በማጠናከር ቴክኖሎጂን፣ ክህሎትንና ዘመናዊ አሰራሮችን ለማስፋፋትና ለማሻሻል በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

በበጀት ዓመቱ ከ192 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ስልጠናውን እንዲወስዱ ታቅዶ እስካሁን ከ100 ሺህ በላይ ዜጎች ስልጠናውን ወስደዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ