+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና የዲጂታል ክህሎትን በማሳደግ በዘርፉ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ያደርጋል- ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ

የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና የዲጂታል ክህሎትን በማሳደግ በዘርፉ ተጨማሪ የአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የሚያደርግ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ገለፁ።

የ''አምስት ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ’’ ስልጠና ሐምሌ 2016 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

መርሃግብሩ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት 5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ዳታ ሳይንስና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት እንዲጨብጡ የሚያስችል ነው።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሹሩን አለማየሁ(ዶ/ር) ፤ ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት ከመሰረተ ልማትና አስቻይ ስርዓት ከመዘርጋት በተጨማሪ የዲጂታል ክህሎት ያለው ማህበረሰብ አስፈላጊ ነው።

ስልጠናውን የተከታተሉ የመንግስት ሰራተኞች ለስራቸው ውጤታማነት እገዛ እያደረገላቸው መሆኑን ጠቁመው፥ አዳዲስ የስራ እድል መፍጠር የቻሉ እንዳሉም ተናግረዋል።

በተጨማሪም የዲጂታል ክህሎትን በማሳደግ በዘርፉ ተጨማሪ የአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንት እንዲመጣ ያደርጋል ብለዋል።

በመርሃግብሩ የሚሰጠው ስልጠና ከዲጂታል ክህሎት በተጨማሪ እውቀትን መሰረት ያደረገና ምክንያታዊ ውሳኔዎችን መስጠት የሚያስችሉ ክህሎቶችን ማግኘት የሚቻልበት እንደሆነም ተናግረዋል።

ስልጠናውን የተከታተሉ ወጣቶች በበኩላቸው ያገኙት ክህሎት ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውና ለስራቸው ተጨማሪ ክህሎትና እውቀት ያስጨበጣቸው መሆኑን ገልፀዋል።

ከሰልጣኞቹ መካከል ወጣት ዲቦራ የኔሰው እንዳለችው፥ ስልጠናው በነፃ የሚሰጥና ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ በመሆኑ ሁሉም እድሉን መጠቀም አለበት ብላለች።

ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ፅዮን ዘለቀ በበኩሏ፥ ስልጠናው ሳቢ በሆነ መልኩ የሚሰጥና ተጨማሪ የስራ እድልን ለማግኘትና ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ገልፃለች።

#ኢዚአ

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ