+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

780 ሺህ ዜጎች የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን በመውሰድ ላይ ናቸው - ዶ/ር በለጠ ሞላ

በ5 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በአጠቃላይ በሀገሪቱ እስካሁን 780 ሺህ ዜጎች የኮደርስ ስልጠናውን እየወሰዱ እንደሚገኝ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ከዚህም ውስጥ 280 ሺህ የሚሆኑት ተመርቀው ሰርተፍኬታቸውን መውሰዳቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ይህ ሰርተፍኬት ዓለም አቀፋዊ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

ይህ ፕሮግራም የሶስት አመት ፕሮግራም ሲሆን በነዚህ አመታት ውስጥ ከ5 ሚሊየን እስከ 7 ሚሊየን የሚሆኑ ወጣቶች የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ዓለም ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ስርአት ውስጥ እየገባች ትገኛለች ያሉት ሚኒስትሩ፤ እንደ ሀገር ዜጎች የበቁ ሆነው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ አምራች እንዲሆኑ ኢኒሼቲቩ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም፤ በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን ሽግግር ለማሳካት የተለያዩ ስትራቴጂዎች ተነድፈው ወደ ተግባር መገባቱን ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚን ሽግግርን እናሳካላን ሲባል የተለያዩ ግብአቶችና ስራዎች ይጠበቃሉ ያሉት ሚኒስትሩ፤ አንዱና ዋነኛው የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ማስፋፋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የጀመረችውን ይህን ውጥን እውን ለማድረግ መንግስትና የግሉ ማህበረሰብ በጋራ መስራት እንዳለባቸው የገለፁት ሚኒስትሩ፤ በዚህም ረገድ በርካታ ለውጦች እንደተመዘገቡ ጠቁመዋል፡፡

የኢንተርኔትና ሞባይል ተጠቃሚ ቁጥርን በማሳደግ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አስቻይ የሆኑ ግብዓቶችን መስራትና ማሳደግ ዋነኛው የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ዓላማ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

የዜጎችን የዲጂታል አቅም ለመገንባት የሰው ሀብት ልማት ላይ መስራትም እንደሚያስፈልግም ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ